

ቤተሰብ
<< እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ።
እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል።
ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩም ነበር።
አዳምም ለሚስቱ ሔዋን ብሎ ስም አወጣ፥ የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና። >>
ይህ ከላይ ያነበብነው ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዘፍጥረት ምዕራፍ 1 2 እና 3 ላይ የምናገኘው ቃል ነው እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት ቢደሰትም አንድ ደስተኛ ያልሆነበት ነገር ነበረው ይኸውም በፈጠረው ሰው ብቸኝነት ነበር፥ ስለዚህ የሰውን ብቸኝነት የሚያስወግድበት ብቸኛው መንገድ የአዳምን ስጋና አጥንት የሚመሳሰል ሴት ሰርቶ ለአዳም ረዳት ማድረግ ነው ።
አዳምም በሁሉም ላይ ስም የማውጣት ስልጣን ተሰጥቶት ስለነበር አጠገቡ ላገኛት ረዳቱ ስም ሲሰጥ ሴት ትባል አለ። ስም ሲያወጣላትም ሔዋን ነው ያላት ለምን አበበ - ከበደ - አለሙ - አላለውም ??
ይቀጥላል ..
ካሱ ቦስተን