top of page

ሕይወት ያለው   .  .  

.  ሕይወት  የሌለው

 

     ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም፡፡ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ፡፡ በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል፡፡ የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን፡፡    1ኛዮሐ.5፣12-15

 

   የእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሐዋርያው ዮሐንስ በመጀመሪያው መልዕክት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ በምድር ላይ ያሉትን ሰዎችን በሁለት ከፍሎ አስቀምጧቸዋል፡፡

 

    የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የግል አዳኛቸው አድርገው በመቀበል እርሱን የታመኑና እርሱ ያላቸው ሲሆኑ

   ሁለተኛዎቹ ደግሞ ይህንን ሕይወት አንፈልግም ያሉና የማያምኑ ጌታ ኢየሱስን የግል አዳኛቸውና ጌታቸው አድርገው ያልተቀበሉ ናቸው፡፡

 

   የመጀመሪያዎቹ ኢየሱስ ያላቸው ሰዎች ልጁ ያላቸው ሕይወትም ያላቸው ናቸው፡፡ በኢየሱስ አምነው የዳኑ ሕይወት አላቸው፡፡ ሕይወታቸውም የዘላለም ነው ለዘላለም ከማይሞተው ጌታቸው ጋር ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉ ምንኛ የታደሉ ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ አይደለም የሚለው በዚህ ጌታ ያመኑና የታመኑ እንደ ፈቃዱ አንዳች ቢለምኑ/ቢጠይቁ ጌታቸው ይሰማቸዋል ፡፡ የሚለምኑትንም ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚሰማላቸው ቢያውቁ ቢያምኑ የለመኑት ወይንም የጠየቁትን እንደተቀበሉ ያውቃሉ፡፡ ምክንያቱም አምላካቸው ከእነርሱ ጋር ነው ከእነርሱ ጋር የሆነው ደግሞ አምላካቸው ነውና ይሰማቸዋል ይመልስላቸውማል፡፡

 

    ሁለተኛዎቹ አይነት ሰዎች ደግሞ ልጁ የሌላቸው ሕይወት የሌላቸው በምድር የተሳካላቸው ቢመስሉ እንኳ ለዘላለም ሞት የታጩ ሕይወት የሌላቸው ሆነው የሚመላለሱ አሳዛኝ የሰው ልጆች ናቸው፡፡

ወዳጄ አንተ አንቺ ከየትኛው ወገን ነህ ነሽ ? ዛሬ በትክክል መልስ ስጥ/ስጪ ኢየሱስ አለህ/አለሽ ? እርሱን በሕይወትህ/በሕይወትሽ አንግሰሃል/አንግሰሻል ? ለመሆኑ ይህ ጥያቄ ገብቶሃል/ገብቶሻል ? ኢየሱስ በሕይወትህ/በሕይውትሽ አለ? እርሱን የግል አዳኝህ/አዳኝሽና ጌታህ/ጌታሽ በማድረግ ተቀብለኸው/ተቀብለሽው በሕይወት ነው የምትመላለሰው/የምትመላለሺው ? እርሱን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመንህ/በማመነሽ የዘላለም ሕይወት እንዳለህ/አንዳለሽ ታውቃለህ ታውቂያለሽ ? እንደዛ ከሆነ መልካም ነው የታደልክም/ሽም ነህ/ነሽ ፡፡

 

    ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ ነው ያለው፡- በእርሱ በማመንህ እርሱ አለህ እርሱ ዘላለማዊ ነውና የዘላለም ሕይወት አለህ እንዲሁም በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ፡፡ በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል፡፡ የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን፡፡


    በእርሱ ካላመንክ/ካላመንሽ እርሱን የሕይወትህ/የሕይወትሽ አዳኝና ጌታህ/ጌታሽ አድርገህ/አድርገሽ ካልተቀበልክ/ካልተቀበልሽ አሁንም በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ካለህ/ካለሽ ዛሬ ወስን/ወስኝ ሕይወት ይሻልሃል/ይሻልሻል፡፡  ለምን ይህንን ሕይወት ችላ ትላለህ/ትያለሽ ?

የእግዚአብሔር ቃል በዮሐንስ 3፣14-18 ላይ

   ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።

   እንደገናም  በዮሐንስ 3፣ 36 ላይ በልጁ (በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ) የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ (በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ)  የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። እንግዲህ ቃሉ ይሄንን ይላል ስለዚህ ወዳጄ የሄንን ታላቅ የምስራች ዛሬ ስትሰማ/ስትሰሚ ምን ተሰምቶህ/ተሰምቶሽ ይሆን?   

 በእርሱ  ያመኑ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ አላቸው ይህ ብቻ ሳይሆን ሕይወትም ለዛውም የዘለዓለም ሕይወት አላቸው እርሱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር አለና ሁሌም ይሰማቸዋል፡፡

 

   ስለዚህ ወደዚህ ሕይወት እንድትመጣ/እንድትመጪ እን ጋብዛችኋለን፡፡ እርሱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የኃጢአትሀን/የኃጢአትሽን ዋጋ በመስቀል ላይ በመሞት ከፍሏል፡፡

 

ስለዚህ ወንድሜ እህቴ ሕይወት ይሻልሃል፡፡ ሕይወት ይሻልሻል፡፡

 

    ወደዚህ ጣፋጭ ወደሆነ ሕይወት መምጣትና ለመቀላቀል ውሳኔ አድርጋችሁ ከሆነ ይህንን ጸሎት እንድትፀልዩ  እንጠይቃችኋለን፡፡

 

   እግዚአብሔር ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ስለሆንኩ ምሕረትህ ያስፈልገኛል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኔ ክቡር ደሙን እንዳፈሰሰና እንደሞተ አምናለሁ አሁን  ኢየሱስ ክርስቶስን ልቤንና መላው ሕይወቴን እንዲለውጥ የግል አዳኜ  አድርጌ እቀበላለሁ ፡፡

 

          የሄንን ጸሎት በጸለያችሁበት ቅጽበት የእግዚአብሔር ልጅነት ስልጣንን አግኝታችኋልና ደስ ይበላችሁ ፡፡ 

  

    የእግዚአብሔር ቃል በዮሐንስ ወንጌል 1 : 12 ላይ ለተቀበሉት ሁሉ ግን በሰሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ  የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው ይላልና ፡፡ 

 

    ወንድሜ እህቴ ከዚህ በኋላ ልታደርጉ የሚገባችሁን ማለትም እንዴት መጽሐፍ ቅዱስን ልታነቡ እንደምትችሉና እንዴት ከወገኖች ጋር ህብረት ማድረግ  እንዳለባችሁ እንዲሁም የተለያየ ጥያቄ ቢኖራችሁ በአድራሻችን ልታገኙንና ልንወያይ እንችላለን፡፡

    

     የእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት ከናንተ ጋር ይሁን

bottom of page