top of page

ቅዱሳን ሁኑ 

ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።  (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት1:15-16)  

(ትንቢተ ሕዝቅኤል 36:20-23)

 

ወደ መጡባቸውም ወደ አሕዛብ በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነርሱን፦ ከምድሩ የወጡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እነዚህ ናቸው ሲሉአቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ። እኔ ግን የእስራኤል ቤት በመጡባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሱት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ራራሁላቸው። ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በመጣችሁባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እናንተ የምሠራ አይደለሁም። በአሕዛብም ዘንድ የረከሰውን፥ በመካከላቸው ያረከሳችሁትን ስሜን እቀድሰዋለሁ፤ በዓይናቸውም ዘንድ በተቀደስሁባችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፡፡

 

     እግዚአብሄር እኔ በአህዛብ ፊት እናንተን የምሰራው  ከነርሱ ውጡና የተለያችሁ ሁኑ እርኩሱንም ነገር አትንኩ ብያችሁ ነበር ነገር ግን እናንተ በመሃከላቸው ሆናችሁ ቅዱሱን ስሜን አረከሳችሁት: ስለዚህ እኔ እንደሎጥ እራራላችሁና እጃችሁን ይዤ አወጣችኋለሁ ለራሴ ለቅዱሱ ስሜ ስል እቀድሳችኋለሁ: ያኔ እናንተን ስቀድስ መልካም አድርጌ ስሠራችሁና በናንተ ውስጥ ስኖር አህዛብ እኔ እግዚአብሄር እንደሆንኩ ያውቃሉ እኔ እራሴ ስሜን አስከብራለሁ እናንተን እቀድሳለሁ እንደገናም በእናንተ እቀደሳለሁ ይላል ይህን የማደርገው ግን እናንተ ስለሰራችሁት ስለመልካም ስራችሁ ሳይሆን ስለራሴ ቅዱስ ስለሆነው ስሜ ነው ይላል ምክኒያቱም እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን እንድትሆኑ ስለምፈልግና እኔንም ማየት የምትችሉት በቅድስና ስትኖሩ ስለሆነ ነው፡፡

 

   እንግዲህ መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ እንድትሰሩና እኔ እንድኖርባችሁ ይህን ከዚህ የሚቀጥለውን በመካከላችሁ አደርጋለሁ ይላል እግዚአብሄር፡፡

 

     ከአሕዛብም መካከል አወጣችኋለሁ፥ ከየአገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ወደ ገዛ ምድራችሁም አመጣችኋለሁ። ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፥ እናንተም ትጠራላችሁ፥ ከርኵሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ። አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ፥ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፥ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፥ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ። ለአባቶቻችሁም በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ፤ ሕዝብም ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ። (ትንቢተ ሕዝቅኤል 36:24-28) አሜን አሜን አሜን!!!

አናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ !

 

    “ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤ ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። (ኤፌሶን 5:8-13)።

    የእግዚአብሔር ቃል እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ ሲል ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር የተሰተካከለ የጽድቅ እምነት ያገኝነው እኛ ክብርን፤ሕይወትንና ኃይልን ከእርሱ በቀጥታ ተቀብለን አለምንም መከልከል ስለምናስተላልፍ ነው አለም ክርስቶስን የምታየው በኛ ነውና አለበለዚያ ግን የአለም ብርሃን ሳንሆን የጋን መብራት ነው የምንሆነው ። በዚህ አለም በምንኖርበት ጊዜ በኑሯችን ሁሉ ብርሃን መሆን አለብን። “የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ናቸውና” (የሉቃስ 16:8)። ወገኖቼ እኛ ከነርሱ ይልቅ ልባሞች መሆን ይገባናል። አባታችንን መምሰል። እንደ ብርሃን ልጆች በብርሃን፥ በጥበብ፥ በእዉቀት በምህረት፥ በርህራሄ፥ በፍቅርና በጽድቅ መመላለስ ይኖርብናል። ክርስቶስ የአለም ብርሃን ነው። በብርሃኑ ብርሃን እናያለን። እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ነን። የክርስቶስን ጽድቅ ለብሰናል። በፍቅር እንኑር። በቅድስና እንኑር። ወንንጌልን እንስበክ። ህይወቱ በህይወታችን ይገለጥ። ጌታ ራሱ “እናንተ የአለም ብርሃንና አለሙን የሚያጣፍጥ ጨው ናችሁ ብሎናል። ብርሃን ናችሁ ካለ ብርሃን ነህ፥ ብርሃን ነሽ እንጂ አሁድ እሁድ እየተሰባሰብን ክርስትና ክርስትና የምንጫወት አይደለንምም መሆንም የለብንም። ቃሉ የታመነ ነው።

   መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን “እግዚአብሔር እርሱ ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም።” (1ዮሐ. 1፡5) ብርሃን የሕወት፣ የተስፋ፣ የእውቀት፣ የጽድቅ... ወዘተ ምልክት ነው። ጨለማ ደግም የሞት፣ የተስፋ መቁረጥ፣ የድንቁርና፣ የሃጢያት... ወዘተ ምልክት ነው። እግዚአብሔር ባለበት ሁሉ ያለው ሕይወት ነው፣ ተስፋ ነው፣ ጽድቅ ነው፣ መገለጥ ነው። እግዚአብሔር እርሱ ብርሃን ነው ደግምም በብርሃን ውስጥ ይኖራል። 

   በወንጌል በማመን የእግዚአብሔርን ሕይወት ስንካፈል በእግዚአብሔር ብርሃን ውስጥ እንገባለን። በዚህ ብርሃን ውስጥ ስንሆን ሞት አያስፈራራንም። ይህ ብርሃን ባለበት ጨለማ ስፍራ የለውም። ብርሃኑ በጨለማ ይበራል። ይህ ብርሃን የሚዋጋንን ማንኛውንም የጨለማ ሃይል ይገልጣል። ብርሃኑ ሲገዛ ጨለማው ስፍራ ይለቃል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ብርሃንና ጨለማ አብረው ሊቆሙ አይችሉም። በእግዚአብሔር ብርሃን እየተመላለስን በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ለመግባት አንችልም። በእግዚአብሔር ብርሃን ውስጥ እያለን በሃዝንና በትካዜ ውስጥ አንሰነብትም። ዳዊት እንደዘመረው እግዚአብሔር ብርሃናችን ሲሆን የሚያስፈራን፣ የሚያስደነግጠን አይኖርም። (መዝ. 27፡1) 

 

ስለዚህ ዛሬም እራሳችንን የምናይበት የእይታ መነጽር ይስተካከል እላለሁ ተባረኩልኝ ሳምንት በክፍል 14 እንገናኝ ቸር እንሰንብት አሜን አሜን ፡፡

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ !

   

       እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።

ማቴዎስ 5፡13

      የሰው ልጅ ጨውን ለብዙ መቶ ሺህ ዓመታት ለተለያየ አገልግሎት ሲተቀምበት ኖሯል አሁንም እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡  ጨው በዓለም ላይ የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ከ14,000 በላይ ለሚሆኑ የተለያዩ አገልግሎቶች መዋሉን ሰለጨው ጥቅሞች በተለያዩ ድህረገጾች ላይ ተገልጾ ይገኛል፡፡ 

 ስለጨው ጥቅምና ጉዳት ለመዘርዘር ሳይሆን ለምንድነው ጌታ እኛን በጨው የመሰለን ? ለዚያውም የምድር ጨው ናችሁ ሲለን ምን ለማለት ፈልጎ ነው?  የሚለው ነጥብ ላይ ማተኮር ያስፈልገናል ስለዚህ በትንሹ ጨው ለምግብ ከሚሰጠው ጥቅም ጋር አያይዘን እንመልከተው ፡፡ 

ምግብ ለመበላት ሊጣፍጥ ይገባዋል፡፡ ምግብ የማይጣፍጠው ከሆነ ሰው ለመብላት አይበረታታም፡፡ ምግብን ለማጣፈጥ የሚጠቅመው ዋነኛው ነገር ደግሞ ጨው ነው፡፡ ጨው የምግብ ጣእምን ሰብሰብ የማድረግ አቅም አለው፡፡ ጨው የምግብ ጣእምን ወደ አንድ ደረጃ የማምጣት ችሎታ አለው፡፡  ጨው ምግቦችን ጣዕማቸው ሳይቀይር የማቆየት ብቃት አለው፡፡ ጨው የሚስብ ነገር አለው፡፡ ጨው በሁሉ ሰው ታዋቂና ተፈላጊ ጣእም አለው፡፡ ጨው በሁሉም አይነት ምግቦች ላይ ቀይ ወጥ: አልጫ ወጥ: ጎመን ወጥ: ሰላጣ: ፍርፍር: ወ.ዘ.ተ. ጨው የማይገባባቸው የምግብ አይነቶች የሉም፡፡ ምንም ያህል ድግስ ተደግሶ የሚያጣፍጥ ጨው ከሌለው ድግሱ ተመጋቢ ያላገኘ ድግስ ይሆንና የተዘጋጀው ምግብ ወደቆሻሻ መጣያ ስፍራ መወሰዱ አይቀሬ ነው ፡፡ ልክ ከእግዚአብሄር ጋር በክርስቶስ የመስቀል ስራ እንደታረቅን ወደ መንግስተ ሰማያት ያልገባነው በምድር ላይ ወሳኝ ስራ ስላለን ነው፡፡ ስለ   እኛ ስለተከታዮቹ ኢየሱስ ሲናገር የምድር ጨው ናችሁ ይላል፡፡

     ጨው የምግብን ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው እኛ የምድርን የህይወት ደረጃ ከፍ እናደርገዋለን፡፡ እኛ እግዚአብሄርን የመፍራት ከፍ ያለ የህይወት ደረጃ ካላሳየን ምድር እግዚአብሄርን ፈርቶ የሚያስፈራራው ምሳሌ አይኖረውም፡፡ እግዚአብሄርን የመምሰል ህይወት ምሳሌ ካልሆንን ምድር የእግዚአብሄርን መልክ ማየት አትችልም፡፡ እኛ እግዚአብሄርን ስለማክበር ሞዴል ካልሆንን አለም እግዚአብሄር እንዴት እንደሚከበር ምንም ፍንጭ አይኖረውም፡፡ በእግዚአብሄር ፀጋ በራስ የማይቻል ነገር በማድረግ እግዚአብሄር እንዳለ ካልመሰከርን ስለእግዚአብሄር መኖር የሚመሰክር ሰው አይኖርም፡፡ 

ጨው የምግብን የተለያየ ጣእም እንደሚሰበስበውና አንድ ወጥ ጣእም እንደሚሰጠው እኛም የምድርን ትኩረት ወደ ሰማይ የምናመለክተው እኛ ነን፡፡ እንዲሁም ከሞት በኋላ ህይወት አንዳለ አድርገን በመኖር ሌሎችንም የምናነቃውና ምድራዊ ህይወት ጊዜያዊ እንደሆነ አድርገን በመኖር ሌሎቹ ለዘላለማዊ ህይወት እንዲዘጋጁ የምናስጠነቅቀው እኛ ነን፡፡ በሰማይ ጌታ እንዳለው ሰው በመኖር ራስን በመግዛትና በዲሲፒን ኑሮ ክርስትና እንደሚቻል ፣ እግዚአብሄርን ማስደሰት እንደሚቻልና ለእግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ መኖር እንደሚቻል ለሌሎች ምሳሌ የምንሆነው እኛው ነን፡፡

    ሰው በእግዚአብሄር አምሳል እንደተፈጠረና ለእግዚአብሄር ክብር እንደተሰራ በህይወታችን የምናመለክተው እኛ ነን፡፡  እግዚአብሄርን ማክበር የሰው በምድር ላይ የመፈጠር አላማ መሆኑን የምናስታውሰው እኛ ነን፡፡ ምድርን ከሚታይ ነገርና ከስጋዊ ፍላጎት ከፍ ያለን ደረጃ የምንሰጣት እኛ የምድር ጨው ነን፡፡ በምድር ላይ የእግዚአብሄር ልጅ ሆኖ ስለመኖር ለሌሎች የምንመሰክረው እኛ ነን፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሄርንና ሰውን በመውደድ እንዴት እንደሚኖር የምንመሰክረው እኛ ነን፡፡

    ጨው ክብሩ ለምግብ ጣእም መስጠቱ ነው፡፡ የጨው ክብሩ ኮስታራነቱ ነው፡፡ እኛ ነን አለምን ማጣፈጥ የምንችለው፡፡ አለምን ለማጣፈጥ ጣእሙ ያለን እኛ ነን፡፡ እኛ ግን ይህንን ወሳኝ ሃላፊነታችንን ካልተወጣን ማንም ሊሰራልን አይችልም፡፡ እኛ አለምን ካላጣፈጥን እኛን ሊያጣፍጠን የሚችል አለም የለም፡፡ ጨው ደግሞ ካላጣፈጠ ለምንም አይጠቅምም፡፡

    ስለዚህ ነው ጨው በአለም ሁሉ መበተን ያለበት፡፡ ጨው በጨው እቃ ውስጥ ቢቀመጥ ምንም እንደማይጠቅም ሁሉ እኛም በየሰንበቱ መሰባሰባችንና ክርስትና ክርስትና ማለታችን ለሌላው ካልጠቀመ በጨለማው ላይ ካላበራና ለመራራው አለም ጣዕም ካልሰጠ ጠቃሚነቱ የማይታየው፡፡ ጨው ግን በተለያየ አይነት ወጥ ውስጥ ቢጨመር ያጣፍጣል ምግብ በሰሃን ተቀምጦ አጠገቡ በጠርሙስ ጨው መቀመጡ ምግቡን ሊያጣፍጠው እንደማይችል ነገር ግን  ከጠርሙሱ ውስጥ ወጥቶ ሊበተን እና ሊነሰሰነስ ይገባዋል ፡፡ ስለዚህ ክርስትያኖች የምንሰበሰበው ለመበረታታት ፣ ለመሞረድ ፣ ለመታደስ እና ለስራ ዝግጁ ሆነን ለመበተን እንጂ ስራው በምድር ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወት ውስጥ ነው፡፡ ጨውነታችን በትምህርት ቤት ፣ በሆስፒታል ፣ በየፋብሪካውና በየኢንዱስትሪው በየስራ ስፍራችና በየሰፈራችን፣ በሃገር አስተዳደር ፣ በውትድር ፣ በንግድና በመሳሰሉት ሙያዎች ሁሉ ይፈለጋል፡፡

    እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም። ማቴዎስ 5፡13

    ክርስትናን ካለራስ ወዳድነት በፍቅር ለሌሎች መልካም ምሳሌ በመሆን ክርስትናን እንዲቀበሉ የምናበረታታው የምድር ጨው በመሆን ነው፡፡ ስለዚህ መንፈሳዊ ቤት ሆኖ መሰራት አንዱ ለዚህ መራራ ለሆነው አለም ጣዕም ለመስጠት ነውና  እንግዲህ እኛ የምንጠቀምበት ጨው ጨው ሆኖ ከማገልገሉ በፊት ብዙ ሂደቶችን አልፎ ነውና ለማጣፈጫነት የዋለው እኛም አለምን ለማጣፈጥ በእግዚአብሄር ቃልና በጸሎት እንዲሁም በሃይሉ ችሎት እየበረታንና እየተሰራን እንድንዘጋጅ መሰራታችንን እንቀጥል እላለሁ ተባረኩልኝ

ህይህ.jpg

ይህ ጤና ይስጥልኝ የተሰኘ የሚዲያ አገልግሎት ነው፥ አዘጋጆቹ (ካሳሁንና ኤልሳ) ጤና እንዲሆንልዎትና እንዲሳካልዎት እየተመኘን በውስጥና በውጭ አካልዎ ጤንነት ላይ ያተኮረ መረጃና ምክር እንዲሁም ትምህርቶችን ይዘንልዎ የምንቀርብበት መስመር ነው፥ እንዲከታተሉት እንዲያደምጡትና ለወዳጅ ዘመዶችዎ እንዲያካፍሉት እየጠየቅንዎት ተከታታይ ቪዲዮዎችን እንዲያገኙ ሰብስክራይብ የሚለውን ምልክት እና የደውል ምልክቱን መጫንዎን አይርሱ። ከተመቸንዎ ከኛ ጋር ለመቀጠል ሰብስክራይብ የሚለውን ተጭነው የደውል ምልክቱን ቢነኩት ቪዲዮ በለቀቅን ቁጥር መልዕክት ይደርስዎታል። ከኛ ጋር ይቆዩ !! እናመሰግንዎታለን ። ጤና ይስጥልኝ ሚዲያ አገልግሎት ! ኤልሳ ና ካሱ 

 

Video link

UCXQeAJgDLecjaAb_7ZjJmoA

close up full body of speed racing pigeo
The bell.jpg
Amharic Bible (4).JPG

    በዩቲዩብ መስመራችን ሊያገኙን ከፈለጉ  

   እንኳን ደህና መጡ !

በዚህ ድህረ ገጽ ላይ እግዚአብሔር በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሰዎች ሁሉ ያደረገውን መልካም የማዳን መንገድን የምናይበትና የምንማማርበት የማንንም ቤተአምልኮ የማይወክል መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገና እውነትን የምናይበት የመማማሪያ ድህረ ገጽ ነው ።

 

  •     አላማችን 

 

       በዚህ  ድህረ ገጽ ላይ ሰዎች ሁሉ

 

          በጌታ ኢየሱስ   በኩል

የተፈጸላቸውን የማዳን  ሥራ ተረድተው

    ወደ እግዚአብሔር   መንግስት ፊታቸውን ዘወር

           እንዲያደርጉ    የመንግስቱን

 

    የወንጌል የምስራች   ማቅረብ ነው ።

 

          ኢየሱስ ይወድሃል/ይወድሻል 

 

እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።     (ትንቢተ ኤርምያስ 4:4) 

 አዘጋጅና አቅራቢዎች  ካሣሁንና ኤልሳ 

                                                         (​Kasselsa)Boston                      Since Sep. 2016 

Edited%20Image%202016-02-04%2021-04-12_e
bottom of page