top of page

በድምጽ (በጉሮሮ) ላይ ተጽዕኖ የሚያመጡ መጠጦች

Kitchen Shelf
Egg Delivery
Image by Giorgio Trovato

     ይህ ጽሁፍ ረጅም ሰዓት ለሚያስተምሩና ለሚዘምሩ ወገኖች በድምጽ (በጉሮሮ) ላይ ተጽዕኖ ሊያመጣባቸው ይችላል በሚል ሊወገዱ የሚገባቸው መጠጦች ከብዙዎቹ በጥቂቱ እነዚህ ናቸው ተብሎ ይታሰባል

1. አረንጓዴ ሻይ (green tea ) - ይህ ድምጽ የሚፈጠርባቸው አካባቢዎችን የማድረቅና የመሰነጣተቅ ባህሪ ስላለውና በተፈጥሮ በተለያዩ የውስጥ ሰውነታችን ላይ ያለውን እርጥበት እንዲቀንስ ስለሚያደርግ እንዳይጠጣ ይመከራል::

2. ወተት (milk ) - ወተት በጉሮሮአችን እና በአፍንጫችን መንገድ ላይ ከፍተኛ የወፍራም ምራቅ ወይም (አክታ) ክምችትን ስለሚያስከትል ለድምጽ አወጣጥ ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል::

3. የበረዶ ውሃ (Ice cube/chips) - የቀዘቀዘ ውሃ እየጠጣን ማስተማርም ሆነ መስበክ ወይም መዘመር ለድምጽ መልካም ያልሆነበት በድምጽ መፈጠሪያ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች በቅዝቃዜ ስለሚኮማተሩና ድምጽ ለማውጣት ያለው ጫና እንዲሰነጣጠቁ ያደርጋቸዋልና የሞቀ ሻይ ቢጠጣ (preferably peppermint or licorice root tea; both are fabulous.) መልካም እንደሆነ ይመከራል

4. ጋዝ ያላቸው መጥጦች(ኮካ ፔፕሲ አምቦ ውሃ ... ) እነዚህ መጠጦች በሆዳችን ውስጥ ጋዝ ማለትም አየር ይፈጥርና እየሰበክንም ይሁን እየዘመርን ከሆዳችን ውስጥ በከፍተኛ ግፊት ወደ ድምጽ ማውጫ ጉሮሮ ይመጣና በድምጽ አወጣጥ ላይ ችግር ይፈጥርብናል እንደገናም የሆዳችንን ጡንቻ ዘና አድርገን በዲያፍራም የሳምባ ጡንቻ ብቻ እየተነፈስን እንዳናስተመር/እንዳንሰብክ ወይም እንዳንዘምር ያደርጉናል::

======///=====

ጨው ጥቅሙና መዘዙ !

«ጨው ሲበዛ ያቅራል ፤ በርበሬ ሲበዛ ይመራል» ይባላል፣ ለሰውና እንስሳ ጠቀሚ ከሆኑ ማዕድናት መካከል አንዱ ጨው ነው፤ የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት(WHO) እንደሚመክረው ከሆነ እያንዳንዱ ሰው በየቀኑ መጠኑ ፣ከ 5 ግራም የማይበልጥ ጨው መመገብ ይኖርበታል። ከዚህም ጋር ተያይዞ፤ ፖታሲየም በቀን 3,5 ግራም ጠቃሚ ነው ተብሎ እንደተመሠከረለት በጀርመን ፤ ለህሙማን ጠቀሚ ምክርም ሆነ ትምህርት ያካፍላል ተብሎ የሚታመንበት ፣ የቤት ሀኪም(ሃውስ አርትዝት)የተሰኘው መጽሔት አስገንዝቦአል።

ጨው ይጠቅማል ብለን ስናወሳ፣ ምን ዓይነት የትኛውን ጨው ማለታችን እንደሆነ በቅድሚያ ግልጽ ማድረግ ሳይኖርብን አይቀርም።

 

ለምግብ ማጣፈጫ ሰዎች የሚጠቀሙበት የተለመደው ማዕድን ጨው ፣ በሥነ-ቅመማ ስሙ «ሶዲዮም ክሎራይድ» (NaCl)የተሰኘው ነው። ጨው፤ ሳይጣራ እንዲሁ የባህሩን ከውሃ ጋር የተቀላቀለውን በማቅረብ ባልተጣራ መልኩ ወይም አጣርቶ ማቅረብ ይቻላል። ለጤንነት ይበልጥ ተፋላጊ የሆነውና ሃኪሞች በሚያሳስቡት መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀው ፣ አዮዲን (አዮዳይን)የተሰኘው ሌላ ማዕድን የተቀላቀለበት ነው። ለአንስሳትና ሰዎች ህልውና እጅግ ጠቃሚ መሆኑ የሚነገርለት ጨው፤ ሲበዛ ለተጠቀሱት ክፍሎች ባቻ ሳይሆን ለዕጽዋትም ጎጂነቱ ከቶውንም አያጠራጥርም። የተመጠነ ጨው፤ ምግብን አጣፍቶ ለሰውነት ለአጥንትም ሆነ ለደም የሚጠቅም መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምግብ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ ተጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግም ፍቱንነቱ የሚያጠራጥር አይደለም።

ጨው ፣ በዓለም ህዝብ ታሪክ፣ ለምግብ ማጣፈጫነት የረጅም ዘመናት ታሪክ ነው ያለው። ሰው በቅድሚያ በሠፈረባቸውና ሥልጣኔ ባሥፋፋባቸው የዓለም ክፍሎች ብቻ ሳይሆን፤ በማዕከላዊው አውሮፓ በምትገኘው ጀርመን እንኳ፤ የ 3,100 ዓመታት ታሪክ ያለው መሆኑ ነው የተገለጠው። የጀርመን ዛኽሰን አንሃልት ፌደራል ክፍለ ሀገር፣ በቁፋሮ የጥንት የሥልጣኔ አሻራዎችን የሚያስሱ ጠበብት ባልደረባ የሆኑት ሃራልድ ሜለር ፤ ሐምሌ 9 ቀን 2005 ጥንታዊውን የጨው ማዕድን ማውጫ ቦታ ለተመልካቾች በማሳየት እንደገለጡት ከሆነ፣ በሃለ ከተማና አካባቢዋ ይኖር የነበረው ህዝብ ፤ «ነጩ ወርቅ » የሚል ተቀጥላ ስም አግኝቶ በነበረው ጨው ሳቢያ ፣ ለሺ ዓመታት በተሻለ የኤኮኖሚ ደረጃ ላይ ለመገኘት በቅቷል።

በኢትዮጵያ፣ በተለይ በአፋር በረሃ በዳሉልና አካባቢው የሚገኘው ጨው ፣ እየተጠረበ ፣ አሞሌ ጨው በመባል የታወቀው ጡብ መሰል ጥሬ ጨው፤ በነጋዴዎች አማካኝነት ለደጋው አገር ህዝብ ፣ ከዚያም አልፎ ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች እየተሸጠ፤ ለተጠቃሚዎቹ ተፈላጊ ምርት ፤ ለሻጮቹም ዋና ወረትም ሆነ ንብረት ሆኖ እስከዛሬ ድረስ የንግድ ልውውጡ እንደቀጠለ ነው። ይኸው የጨው ንግድ የ 30 ሺ ዓመታት ያህል ታሪክ እንዳለውም ነው የሚነገረው። የሰሃራ ምድረ በዳ በር ፤ የምሁራንም ዋና ማዕከል የነበረችው ቲምቡክቱ፣ የ 12ኛው ክፍለ ዘመን ነጋዴዎች፤ የጨውን ዋጋ ፣ ከመጽሐፍትና ወርቅ አሳንሰውት አያውቁም ነበር።

በጥንታውያን ግብጾች፤ ሜሶፖታማውያን፤ ቻይናውያን ግሪኮችና ሮማውያን ጨው፤ በተጨባጭነት ለምግብ ማጣፈጫ ብቻ ሳይሆን፤ በጥንታዊ እምነትና ልማድ፤እንዲሆም የተለያየ ሃይማኖች ልዩ ሥፍራ ሲሰጠው ኖሯል።

 

በጥንት ዕብራውያንና ግሪካውያን ዘንድ፤ መስዋዕት ሲቀርብ ፤ በሮማውያን አብያተ መቅደስም ፤ መስዋእቱ በጨው ታሽቶ ነበረ የሚቀርበው። በክርስትና ሃይማኖት፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ደቀመዛሙትቱን፤ «እናንት የዓለም ጨው ናችሁ» ነው ያላቸው። ጨው ፣ ከመበላሸት ፤ኃጢአት ከሆነው ንቅዘት የሚከላከል ፤ የሚያጸዳ ኃይል እንዳለው ሆኖ ነው የሚታየው የሚተረጎመው ማለት ነው። በዘመነ ሐዲስ -ኪዳንም ፤ ጨው በምሳሌና በምልክት፣ የዕውቀት፣ ከንቅዘት ነጻ የመሆን ፤ እንዲሁም በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል ያለ ዘለዓለማዊነትና ሥምረት ተምሳሌት ሆኖ ነው የተወሰደው።

መጽሐፍ ቅዱስ ፤ በአጠቃላይ ፣ ከ 30 በላይ ጨውን የሚመለከቱ ጉዳዮችን አሥፍሯል። እ ጎ አ በ 1933 ዓ ም፤ የቲቤቱ ዳላይ ላማ ሲሞቱ፣ቀጥ ብሎ እንዲቆም በተደረገ ከጨው በተሠራ አልጋ ውስጥ ነበረ የተቀበሩት። በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ፣ በዛሬው ዘመንም ቢሆን የቆየ ልማድ እንዲጠበቅ በሚል ጭምር የሞተ ሰው ከመቀበሩ በፊት፣ ሬሣ- ሣጥኑ ውስጥ አንድ እፍኝ ጨው ይበተናል። ጨው፤ ከኃጢአት ነጻ የመሆን ፣ የዘለዓለማዊነት፣ ዲያብሎስንም ማበረሪያ ምልክት ሆኖ ነው የተወሰደው።

አስማተኞችና ርኩሳን መናፍስት እንዳያበላሹት በሚል ልማዳዊ እምነት እስኮትላንዳውያን በሚጠምቁት ቢራ ላይ ጨው ይጨምሩ ነበር። ለነገሩ የሚጠመቅ ቢራ ሳይበላሽ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆይ ፤ ጨው አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ፤ የሥነ ቅመማው ሳይንስ የሚያረጋግጠው ነው።

በመግቢያችን ላይ በጨረፍታ እንዳነሳነው፣ ለምግብነት የሚውል ጨው አዮዲን ማዕድን ሊኖረው ይገባል። አለበለዚያ ፣ ከአንገት ዕጢዎች (ታይሮይድ ግላንድ )የተባለው በማበጥ ወደ እንቅርት ይለወጣል። ኢትዮጵያ ፣ በያመቱ ከ 313,000 እስከ 399,000 ቶን ጨው እንደምትጠቀም ይታሰባል። በአዮዲን እጥረት በሚከሠት የጤና መቃወስ ሳቢያ ፣ አንዳንድ የዜና ምንጮች እንደሚጠቁሙት፤ በእርግዝና ወቅት፤ 50 ሺ ያህል ሰዎች ናቸው ህይወታቸው የሚያልፈው። በተለይ ህዝብ በርከት ብሎ በሚኖርባቸው በአገሪቱ ደጋማ አካባቢዎችም ሆኑ አምባዎች፤ የአዮዲንና አንዳንድ ጠቃሚ ማዕድናት እጥረት መኖሩ የታወቀ ነው።

 

በአሁኑ ዘመን ጨውን መጠን ባለፈ መልኩ፣ በተለያየ መንገድ ሰዎች እንደሚመገቡትና ይህም የደም ግፊትን ከፍ እንዲል በማድረግ በጤንነት ላይ ሳንክ እየፈጠረ ስለመሆኑ፣ የጤና ሳይንስ ባለሙያዎች ከማስመገንዘብ የቦዘኑበት ጊዜ የለም። ጨው፣ ድንገተኛ የልብ ድካምና ተመሳሳይ ህመም እንደሚያስከትል፣ ብርቲቱ የደም ግፊትም እንደሚያስከትል ነው የሚነገርለት። ከሞላ ጎደል የደም ግፊታቸው ከመደበኛው ትንሽም ቢሆን ከፍ የሚልባቸው ሰዎች የሚመገቡትን የጨው መጠን በአጅጉ መቀነስ ይኖርባቸዋል።

በምዕራቡ ዓለም ፤ በአሁኑ ጊዜ፤ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ፤ የምግብና መጠጥ አዘጋጂ ኩባንያዎች ወይም ታላላቅ የምግብ መደብሮች፣ በየጊዜው የሚቀርበውን ጤና-ነክ መመሪያ ልብ በማለት ፣ የሶዲዬም ፍጆታ መጠን እጅግ ዝቅ እንዲል እርምጃዎችን እስከመውሰድ መድረሳቸው ይነገርላቸዋ። ጨው በይበልጥ የሶዲየም ይዘት ተቀንሶ ፣ የፖታሲዮም ፍጆታ እንዲጨምርም ነው ምክር የሚሰጠው። ፖታሲየም ፤ በመሠረቱ፤ የባቄላ ዝርዮች ከሆኑ ጥራጥሬዎች፤ ከአተር፣ ከለውዝ ዓይነቶች ከ«እስፒናች»፤ ሙዝ ፓፓያና ቴምር ጭምር ይገኛል።

በብዙ አዳጊ አገሮች፤ እጅግ ተፈላጊ ከሆነው ኢምንት የምግብ ዓይነት ይበልጥ እጥረት የሚያጋጥመው ፣ የ «ቪታሚን ኤ»፣ አዮዲንና የብረት ማዕድናት ናቸው።

ጨው በሰውነት ውስጥ እንዴት እንደሚከማች፤ በልዩ ተልእኮ የተረጋገጠበት ሁኔታ አስገራሚም ተብሏል።

 

 በ 1997 ዓ ም፣ ወደ ኅዋ ተጉዘው በነበሩት ጀርመናዊው ጠፈርተኛ ራይንሆልድ ኤባልድ ላይ የተከሠተው እንደ አንድ ማስረጃ ይጠቀሳል። አንዳች የስበት ኀይል በሌለበት ሰውም እንደ ላባ በሚንሣፈፍበት ኅዋ፣ በሰውነት ውስጥ የምግብ ዓይነቶች የሚያሳዩት ለውጥ ምን ይመስላል? ኤባልድ፤ ለ 2 ሳምንት ወደ ኅዋ በበረራ ላይ ሳሉና እንደተመለሱም፤ የሚመገቡትን በዝርዝር መጻፍ ነበረባቸው።

«በበረራው ወቅት፣ በአመጋገቤ፤ በምጠጣውም ጥብቅ ቁጥጥር ነበረ ያደረግሁና የመዘገብሁ። ታዲያ አስገራሚ ሁኔታ ነበረ የተከሠተው። እወስደው የነበረ ው የጨው መጠን ፤ መሬት ላይ ከሚወሰደው ወይም በህክምና መጽሔት ከምናውቀው የተለየ ነበር።»

ጠፈርተኛው የተመገቡት ፤ የጠጡትና የዕዳሪአቸውም ይዞታ በሚገባ ይመረመር ፣ ይመዘን ነበረና አስገራሚ ሆኖ የተገኘው፤ በኅዋው የበረራ ወቅት ብዙ ጨው ሰውነት ውስጥ መጠራቀሙ ነው። አንድ ጤነኛ ሰው፤ ሰውነቱ ውስጥ፣ በ 6 ሊትር ፈሳሽ ነገር ውስጥ ሊኖረው የሚገባ የጨው መጠን ነበረውና!

ተመራማሪዎቹ፣ ጨው በአጠቃላይ በኩላሊት በኩል ተጣርቶ ከሽንት ጋር መወገድ እንደሚኖርበት ቢታወቅም፤ የሰው አካላት ተግባራቸውን ፣ ሁሌ በተለመደው መልክ ብቻ እንደማያከናውኑ ነበረ ተመራማሪዎቹ የተገነዘቡት። ጨው በሰውነት ውስጥ የፈሳሽ ነጥረ ነገርን ዝውውር ማስተካከል ብቻ ሳይሆን፤ ደም ግፊት ላይ ተጽእኖ አለው። በሌላም በኩል፤ በአጥንት ግንባታም መሟሸሽም ረገድ አስተዋጽዖ ያደርጋል። በሽታን የመከላከል ሚናም አለው።ግራም ነፈሰ ቀኝ፤ ይህ ጠቃሚ ማዕድን፣ በሚያስፈልግ መጠኑ እንጂ ከሚገባው በላይ የሚወሰድ ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ጥንቃቄ ያሻል።

=====================

ምስር

ምስር የድም ስኳርን ለመቆጣጠርና ካንሰርን ለመከላከል አንዱ መፍትሔ ሆኗል፡ ምስር ብዙ ፋይበር፣ፕሮቲን፣ዚንክ፣ ብረት፣ ፖታሲየም፣ ፎሌት እና ቫይታሚን ቢ ይዟል፡፡

1. ምስር በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠኖዎን ይቆጣጠራል፡፡ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ምስር ከፍተኛ የፕሮቲንና የፋይበር ይዘት ካላቸው legume family ከሚባሉት ባቄላ፣ አተርና ሽምብራ ቤተሰብ የሚመደብ ድብለ እፀዋት( አባዝርት- አበባ ዝርት) አንዱ ነው፡፡ በምስር ውስጥ ያለው ከፍተኛ ፋይበር የደም ስኳር መጠንን የሚቆጠጠር ነው፡፡ በምስር ውስጥ ያለው ፋይበር በደም የሚመጠጠውን ምግብ ቀስ እንዲል በማድረግ የስኳር መጠንን ወጥ በሆነ መልኩ ይቆጣጠራል፡፡

 

2. በምስር ውስጥ ያለው ከፍተኛ ፋይበር ከዚህ በተጨማሪ ጤናማ የሆነ የምግብ መፈጨት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ይህ በምስር ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን የማይሟሟ ፋይበር በምግብ የመፈጨት ስርዓት ውስጥ ያለውን ውሃ ይመጣል እንዲሁም ቆሻሻን ከምግብ መፈጨት ስርዓት ተሸክሞ ያስወግዳል፡፡ በዚም የተነሳ ምስር ድርቀትን ፣የአንጀት ብግነት በሽታንና ተቅማጥን ለመከላከል ይረዳል፡፡ ይሁንና ከምስር ጥሩ ጠቀሜታ ለማግኘት ምስር ከተመገቡ በኃላ በዛ ያለ ውሃ መጠጣት ይኖርቦታል፡፡ ምክንያቱም ፋይበሩ ብዙ ውሃውን ለመምጠጥ ይቻለዋልና፡፡

 

3. የተላያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እንደ ምስር ያለ ከፍተኛ በፋበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ በልብ በሽታ የመጠቃት አደጋን ይቀንሳል፡፡ ምክንያቱም ምስር በማግኒዝየምና በፎሌት በእጅጉ የበለፀገ ስለሆነ ለልብ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ፎሌት ለልብ በሽታ የሚያጋልጠውን ሆሞሳይስቲን መጠን በመቀነስ የልብ በሽታን ይከላከላል፡፡ ማግኒዚየሙ ደግሞ የደም ፍሰቱን እንዲሻሻል ፣ምግብና ኦክስጂን በመላው ሰውነታችን እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

 

4. ሴሊነም በብዙ ምግቦች የማይገኝ ነገር ግን በምስር ውስጥ ያለ ማዕድን ነው፡፡ ሴሊነም ብግነትን የሚከላከል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን የማያሻሻልና የዕጢ ዕድገትን ለመቀነስ የሚስችል በሽታ ተከላካይ የሆነውን ቲ-ሴል( ቲ -ሕዋስ) የሚያነቃቃ ነው፡፡

 

5. ምስር በብረት የበለፀገ ስለሆነ ካርቦ አይድሬት ቀስ ብሎ እንዲቃጠል እና የሰውነቶ የብረት ክምችትን በመጨመር ሰውነቶ በሃይል እንዲሞላ ያደርጋል፡፡ በተለይ በወር አበባ ጊዜ በብረት ማነስ የሚጎዱ ሴቶች የብረት ክምችታቸውን ያጠናክርላቸዋል፡፡ብረት ሂሞግሎቢን የተሰኘው የደም ሤል ኦክስጅን ወደ ሁሉም ሰውነታችን እንዲደርስ ያግዛል፡፡ ብረት በተለይ ለሚያጠቡና ለነፍሰጡር ሴቶች በጣም ስለሚያስፈልግ ምስርን በታዘውትሩ ይመከራከል፡፡ በተለይ ከቀይ ስጋ በተጨማሪ፡፡

 

6. ምስር በፎሊክ አሲድ የበለፀገ ነው፡፡ ፎሊክ አሲድ ወይም ፎሌት ነፍሰ ጥሩ እናቶች በብዛት እንዲወስዱት የሚመከረ ንጥረ ነገር ነው፡፡ ይህን ንጥረነገር በቀላሉ ከምስር የሚገኝ ነው፡፡ ስለሆነም ነፍሰጡ ሴቶች ምስር በብዛት ቢመገቡ ከወሊድ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል ይረዳቸዋል፡፡

 

7. ምስር ክብደት ለመቀነስ ይረዳዎታል፡፡ ምስር ከፍተኛ ፕሮቲን፣ ፋይበር፣ቫታሚንና ማዕድናት እንደመያዙ መጠን በአንፃሩ ዝቅተኛ ቅባትና ካሎሪስ ስላለው ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

==============================

ለብጉር ማጥፊያ የሚሆኑ ያለሐኪም ማዘዣ የሚሸጡ መድኃኒቶች

ለብጉር ማጥፊያነት የሚያገለግሉ መድኃኒቶች እንደ ያዙት የመድኃኒት ዋና ንጥረ ነገር (Active ingredients) አይነት ብጉርን ከሰውነታችን ላይ በተለያየ መንገድ የሚያጠፉ ሲሆን የተወሰኑት የቡግር ማጥፊ መድኃኒቶች ብጉር ሊያመጡ የሚችሉ ባክቴሬያዎችን የሚገድሉ ሲሆን ሌሎች መድኃኒቶች ደግሞ ከቆዳችን ላይ የተከማቸውን ዘይት የሚያስወግዱ ወይም አዲስ የቆዳ ሕዋሳት ዕድገትን የሚያፋጥኑ እና የሞቱ የቆዳ ሕዋሳትን የሚያሰወግዱ ናቸው፡፡ የተወሰኑት የብጉር መድኃኒቶች ደግሞ እነዚህ ሁለቱንም አጣምረው ይሰራሉ፡፡

1. ቤንዞያል ፕርኦክሳይድ (Benzoyal peroxide):- ይህ መድኃኒት ብጉር የሚያከትለውን ባክቴሪያ ይገድላል፡፡ የቆዳችን ቀዳዳ የደፈነውን የተከማቸ ዘይት እና የሞቱ የቆዳ ሕዋሳትን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ ይህ መድኃኒት የተወሰነ የጎንዮሽ ውጤት ሲኖረው በተለይ ቆዳችሁ ቶሎ የሚቆጣ (Sensitive) ከሆነ የቆዳ መድረቅ፣ መቅላትና ማቃጠል ሊያጋጥማችሁ ይችላል፡፡

2. ሳሊሲይሊክ አሲድ (Salicylic acid):- ይህ መድኃኒት የቆዳችን ቀዳዳዎች እንዳይደፈኑ የሚያደርግ ሲሆን መጠነኛ የሆነ መለብለብና የቆዳ መቆጥቆጥ የመድኃኒቱ የጎንዮሽ ውጤት ነው፡፡

3. አልፋ አይድሮክሲ አሲድ (Alpha hydroxyl acids)፡-ይሄ መድኃኒት ሁለት አይነት ሲሆን አንደኛው ግላይኮሊክ አሲድ(glycolic acid) ሁለተኛው ደግሞ (lactic acid) ይባላል፡፡ አልፋ አይድሮክሲ አሲድ ስኳር ካላቸው የፍራፍሬ አይነት የተሰራ ሲሆን ብጉርን የሚያጠፋው የሞቱ የቆዳ ሕዋሳትን በማስወገድና ብግነትን በመቀነስ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህ መድኃኒት አዲስ ለስላሳ ቆዳ እንዲፈጠር የሚያነቃቃና በብጉር ምክንያት የሚፈጠርን ጠባሳ ያስወግዳል፡፡

4. ሰልፈር (Sulfur):- ይህ መድኃኒት በቆዳ ቀዳዳ ውስጥ ተወትፈው የሚገኙ የሞቱ የቆዳ ሕዋሳትን እንዲሁም ከልክ በላይ የተከማቸን ዘይት ያስወግዳል፡፡ ብዙን ጊዜ ይሄ መድኃኒት ከሳሊሲይሊክ አሲድ፣ ከቤንዞያል ፕርኦክሳይድ እና ሬስኦሪሲኖል ጋር በአንድነት ተዘጋጅቶም ይሸጣል፡፡ የዚህ መድኃኒት የጎንዮሽ ውጤት የቆዳ ድርቀትን ያመጣል እንዲሁም የማይመች ሽታ ያመጣል፡፡

 

=============

አዙሮ መውደቅ (ፌንቲንግ)

በድንገት አዙሮ መውደቅ መንስዔው ብዙ ነው፡፡ ዋና ዋናዎቹም በቂ ደም ወደ አንጎል ያለመድረስ፤ በቂ ደም እየደረሰም ተፈላጊው ኦክስጂንና ምግብ ያለመድረስ ከፍተኛ የደም ግፊትና የስሜት መረበሽ ናቸው፡፡

አንድ ሰው አዙሮት ከመውደቁ በፊት የሚከተሉት የማስጠንቀቂያ ስሜቶችና ምልክቶች ናቸው፡፡

1. ቆሞ ወይም ተቀምጦ እያለ ‹‹መጥፎ ስሜት›› መሰማት፣የማዞር ወይም የማንገድገድ ስሜት

2. የቆሙበት ወይም የተቀመጡበት ቦታና አካባቢው ያለ ዕቃም ሆነ ሰው ዋዥቆ መታየት

3. ማዛጋትና የዕይታ መደብዘዝ

4. የጆሮ መጮህና የስሜት ግራ መጋባት

5. ማቅለሽለሽና ትውኪያ

ከዚህ በኃላ ሰውየው ይወድቃል፡፡በፊቱ ላይ ቀዝቃዛ ላብ ይታያል፡፡ ለጥቂት ሰኮንዶች ወይም ደቂቃዎችም ራሱን ሊስት ይችላል፡፡የደም ግፊቱ ከተለመደው መጠን ዝቅ ይላል፡፤ትንፋሹም በጣም ደካማ ይሆናል፡፡ጡንቻዎቹ በሙሉ ስለሚሰንፉ መንቀሳቀስ አይችልም ፡፡

ስለሆነም አንድ ሰው አዙሮት ሲወድቅ የሚከተሉትን ጠቃሚ ምክሮች ይተግብሩ፦

1. የወደቀው ሰው ተቀምጦ ከሆነ ራሱን በጉልበቶቹ መሀል ዝቅ ማድረግ ፤ጋደም ብሎ ከሆነ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አንድ ጎን ዘንበል ማድረግ፡፡

2. የልብሶቹን ቁልፎች፣ክራቫት፣ቀበቶና የውስጥ ልብሶቹን ማላላት፡፡

3. ፊቱን በቀዝቃዛ ውሃ መርጨት ወይም ፎጣ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ነክሮ በአንገቱ ዙሪያ ማስነካት፡፡

4. በቅርብ ከተገኘ እንዲነቃ አምኒያ ማሽተት፡፡

5. ሕሊናው እስኪመለስ በአፍ የሚሰጥ ነገር ያለመስጠትና ለመቆም አቅም እስከያገኝ ድረስ ጋደም ብሎ እንዲቆይ ማድረግ፡፡

6. በዚህ ካልተሻለ የሕክምና ባለሙያና ማማከር

አዙሮ መውደቅን ለመከላከል የሚከተሉትን ጠቃሚ ምክሮች ይወቋቸው።

1. አዙሮ መውደቅ በረሃብ፣በድካም፣በስሜት መረበሽ የሚነሳ ከሆነ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎችን ማስወገድ፡፡

2. ከመኝታዎ ሲነሱ ወይም ከተቀመጡበት ሲነሱ በአንድ ጊዜ በፍጥነት ብድግ ያለማለት፡፡

3. አልጋው ጫፍ ላይ ለሦስት ደቂቃም ቢሆን ቁጭ ብሎ እግርን እንደተቀመጡ ማንቀሳቀስ፡፡ይህ እንቅስቃሴ በቂ ደም ወደ አንጎል እንዲደርስ ይረዳል፡፡

4. ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ፣ወታደራዊ ሰልፍ ላየወ ወይም ሌሎች አስገዳጅና ማሕበራዊ አጋጣሚዎች ላይ ብዙ ሰዓት በተለይም በፀሐይ ላይ መቆም ካለ እግርን በየተራ ማንቀሳቀስ፡፡

5. በደንገት አዙሮ መውደቅ የብዙ በሽታዎች ምልክት በመሆኑ በቅድሚያ የሚያውቁት ከባድ የጤና ችግር ካለ( የደም ግፊት፣የስኳር በሽታ፣የሚጥል በሽታ የመሳሰሉት ካለብዎ) ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ፡፡

 

 

================================

 

የሮዝመሪ (የጥብስ ቅጠል) ሻይ እንደሚሆን ያውቁ ኖሯል?

አሰራሩ

  • አንድ መካከለኛ ኩባያ ውሃ ማፍላት

  • ውሃው ከፈላ በኋላ ግማሽ የሻይ ማንኪያ የሮዝመሪ ቅጠል (ደረቅ ወይም እርጥብ መሆን ይችላል) መጨመር

  • እሳቱን ቀንሰን ለ5 ደቂቃ ማንተክተክ እና ማውጣት

  • ውሃውን ማጥለል እና የሚቻል ከሆነ ትንሽ ማር ጨምሮ መጠጣት

  • ይሄንን ሻይ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እና በሳምንት ከሶስት ጊዜ በላይ እንዳንጠጣ ይመከራል፡፡

የሮዝመሪ (የጥብስ ቅጠል) ሻይ መጠጣት ለጤናችን ምን አይነት ጥቅም ይሰጣል?

1. ቆዳችን እንዳያረጅ ያደርጋል፡- በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ የሚገኙት ፓይቶኬሚካልስ ቆዳችን እንዳይሸበሸብ ያደርጋሉ፡፡ በብጉር እና በፀሀይ ምክንያት ቆዳችን ላይ የሚፈጠሩ ጥቋቁር ምልክቶች እንዲጠፉ እና ፊታችን እንዲጠራ ይረዳል፡፡

2. የማስታወስ ችሎታን ያሳድጋል፡- በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ የሚገኘው ካርኖሲክ አሲድ የተባለው ንጥረ ነገር የማስታወስ ችሎታችንን በማሳደግ እና የነርቮቻችንን ጤንነት በመጠበቅ የሚታወቅ ነው፡፡ እድሜያችን እየጨመረ በሄደ ቁጥር የሚፈጠረውን የመርሳት ችግር እና ከመርሳት ጋር ተያይዞ የሚመጣውን አልዛይመረስ በሽታ ለመከላከል የሮዝመሪ ሻይ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

3. ካንሰርን ለመከላከል ይጠቅማል፡- በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ የሚገኙት ሮዝማሪክ እና ካፊክ አሲዶች ካንሰርን ለመከላከል ይጠቅማሉ፡፡በተለይ ደግሞ ለትልቁ አንጀት ካንሰር፤ ለጡት ካንሰር እና ለደም ካንሰር መድሃኒት ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ጥናቶች ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡

4. የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል፡- በምግብ አለመፈጨት፤ በሆድ መነፋት፤ እና በሆድ ድርቀት ለሚሰቃዩ ሰዎች የሮዝመሪ ሻይ ፍቱን መድሃኒት ሊሆን ይችላል፡፡ የሮዘመሪ ሻይ አንጀታችን በማረጋጋት የሆድ መነፋት እና ጋዝን ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም በውስጡ ካርነሲክ አሲድ ስላለው በአንጀታችን ውስጥ ያሉትን ጤናማ ባክቴሪያዎች ያበረታታል፡፡

5. የበሽታ መከላከል አቅማችንን ያሳድጋል፡- በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ እንደ ቫይታሚን ሲ፤ ቫይታሚን ኤ፤ ፖታሲየም፤ ማግኒዚየም እና ካልሲየም የመሳሰሉ ለጤንነታችን ጠቃሚ የሆኑ እና የበሽታ መከላከል አቅማችንን የሚያዳብሩ ንጥረ ነገሮች ይገኛሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ቫይታሚን ሲ የበሽታ መከላከል አቅማችንን ከማሳደጉ በላይ በባክቴሪያ እና በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎችን ይከላከልልናል፡፡

6. የአይንን ጤና ይጠብቃል፡- በሳንፈርድ እና በርንሃም የምርምር ተቋሞች የተደረገ አንድ ጥናት እንዳሳየው ከሆነ በሮዝመሪ ሻይ ውስጥ ያለው ካርነሲክ አሲድ የተባለ ንጥረ ነገር የአይናችንን ጤና ይጠብቃል እንዲሁም ከእድሜ ጋር የሚመጣውን የአይን እይታ መቀነስ እነዲስተካከል ይረዳል፡፡

7. የሰውነት መቆጣትን ይቀንሳል፡- የሮዝመሪ ሻይ አንታይ ኢንፍላማቶሪ ነው፡፡ ማለትም በሰውነታችን ውስጥ የሚነሱ መቆጣቶችን/ህመሞችን ያስታግሳል፡፡ በተለይ ደግሞ በጡንቻዎቻችን፤ መገጣጠሚያዎቻችን እና በጅማቶቻችን ላይ የሚነሱ ህመሞችን ለማስታገስ እና ለማዳን ጠቃሚ ነው፡፡

8. የአፋችንን ጠረን ጥሩ ያደርግልናል፡- በአፋችን ውስጥ ባሉ ባክቴሪያዎች ምክንያት የአፋችን ጠረን መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡የሮዝመሪ ሻይ መጠጣት ግን እነዚህን ባክቴሪያዎች ከአፋችን ውስጥ ያጠፋል፡፡ ስለዚህ የአፋችንን ጠረን እና የአፋችን ጤና ይስተካከላል፡፡

9. የስኳር መጠናችንን ያስተካክላል፡- የሮዝመሪ ሻይ ውስጥ ካምፊን፤ ካርኖሶል እና ሉቲሊን የተባሉ ንጥረ ነገሮች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች የልባችንን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያስተካክላሉ፡፡ በተጨማሪም የደም ግፊታችን እንዲስተካከል ያደርጋሉ፡፡

የሮዝመሪ የጎንዮሽ ጉዳት

አንዳንድ ሰዎች ለሮዝመሪ አለርጂክ ሊሆኑ ስለሚችሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ እንደ አስፕሪን ላሉ መድሃኒቶች አለርጂክ የሆነ ሰው ለሮዝመሪም አለርጂክ ሊሆን ይችላል፡፡

የደም ግፊት መድሃኒቶችን፤ የደም ማቅጠኛ መድሃኒቶችን፤ የስኳር ህመም መድሃኒቶችን እና የልብ ህመም መድሃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ የሮዝመሪ ሻይ ከመጠጣቶ በፊት ሀኪም ማማከር ይኖርቦታል፡፡

የሮዝመሪ ሻይ ለእርጉዝ ሴቶች እና ለሚያጠቡ ፍፁም የተከለከለ ነው፡፡

የሮዝመሪ ሻይ የሚጥል በሽታ ላለባቸው ሰዎች አይመከርም፡፡ የነርቭ ወይም የአእምሮ መድሃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ የሮዝመሪ ሻይ ከመጠጣቶ በፊት ሀኪም ማማከር ይኖርቦታል፡፡

 

==========================

 

ከጭንቀት ነፃ (ደስተኛ ሕይወት) ለመኖር ወሳኝ የሆኑ አሥር የሕይወት መርሆች

ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ አሥር የሕይወት መርሆች አውቅ ከሆኑ የሳይኮሎጂ መፅሀፍቶች የተወሰደ እና ከሳይኮሎጂ ባለሞያዎች/አማካሪዎች የተገኘ መረጃ !

ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን ሼር በማድረግ ይጀምሩ፡፡

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።

2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡

4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡

6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡

7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።

8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡

9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡

11. የአዲስ መረጃ ቤተሰቦች፣ ሼር ማድረግ ምን ያህል ደስ እንደሚያሰኝ ስለሚያውቁ ቀናቸውን የሚጀምሩት የኛን መረጃ ሼር በማድረግ ነው፡፡

ደስተኛ ህይወትን ለሁላችንም ይስጠን ! መልካም የጤና ጊዜ!!!

===========================

ኮረሪማና የጤና በረከቱ

የዓለማችን ውዱ ቅመም

ውልደቱ ሕንድ ነው፡፡ ሳይንሳዊ ስያሜው Elettaria ይባላል፡፡

በእንግሊዘኛ Cardamon ወይም Cardamom በመባል ይጠራል ኮረሪማ፡፡ በዓለም ላይ እጅግ ውድ ከሚባሉ እና መልካም ማዕዛ ወይም ጣዕም ካላቸው ቅመሞች አንዱ ነው፡፡ ለብዙ መቶ ዓመታት በባህላዊ ሕክምና ውስጥ ትልቅ ድርሻ ነበረው፡፡ በአገራችንም ከቂቤ ማንጠሪያነት አንስቶ ኮረሪማ ለብዙ ምግቦች ማጣፈጫነት እንጠቀመዋለን፡፡ ይህ ቅመም ከምግብ ማጣፈጫነት በዘለለ በሳይንስ የተረጋገጡ ከፍተኛ የሆኑ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ይነገራል፡፡

1. ካንሰርን ለመካለከል ይረዳል፡- ይህ ትንግርታዊ ቅመም በውስጡ በያዘው አንቲ -ኦክሲደንት ወይም ፀረ-ወክሳጅ ኬሚካላዊ ንጥረነገር የተነሳ የካንሰር መነሾ ሕዋሳትን በመዋጋት ይገታል፡፡

2. የደም ግፊትን ይቀንሳል፡- በልባችንና በሌሎች የሰውነታችን አካላት ዙሪያ ያሉ ውሃዎችን በሽንት መልክ በማስወገድ የደም ግፊት መጠንን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

3. የሰውነት መመረዝን ይከላከላል፡- ሰውነታችን የሚመረዘው ለበአድ ነገሮች ሲጋለጥ ነው ኮረሪማ ደግሞ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ኢንፍላሜሽን ወይም መመረዝ ወይም ብግነትን በመከላከል ሰውነታችን ለዘላቂ በሽታዎች እንዳይጋለጥ ይከላከላል፡፡

4. የጥርስ የጤና እክሎችን ያስወግዳል፡-የጥርስ ኢንፌክሽኖችን ጨምሮ በአፍ ውስጥ የሚፈጠርን መጥፎ የአፍ ጠረን በያዘው ንጥረ ነገር ጋሻነት ያባርራል፡፡ ባይገርማችሁ ብዙዎቹ ማስቲካዎች ሲመረቱ ለጣዕማቸው ኮረሪማን በግብዓትነት ሳይቀር ይጠቀሙታል፡፡

5. ትንፈሳንናየኦክስጂን አጠቃቀምን ያሳድጋል፡- በኮረሪማ ውስጥ ያለው ንጥረ ነገር ወደ ሳንባችን የሚገባው አየር እንዲጨምርና አተነፋፈሳችን እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡

6. ኮረሪማ የጉበትን ጤንነት ለመከላከል፣ የጭንቀት ባህሪያትን ለመቀነስ፣ ክብደት ለመቀነስ፣ ለማቅለሽለሽና ለትውኪያ መፍትሔ ይሰጣል፡፡

7. ፀጉርን የመጠገን ሕክምና ይሰጣል፡- ኮረሪማ አብዝቶ በዕለት ገበታ ውስጥ መመገብ የፀጉር መርገፍና መንጣት ችግርን ከማስወገድ ባሻገር ለፀጉራችን መብዛትና ርዘመት ከፍተኛ አስተዋፆ ያደርጋል፡፡

8. ባክቴሪያ ያወድማል፡-ጥናቶች እንዳረጋገጡት ኮረሪማ 14 የሚደርሱ የተለያዩ ባክቴሪያዎችን ያወድማል፡፡ ኮረሪማ አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች የተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅማቸው ከመጨመሩ ባሻገር ሰውነታቸው ባክቴሪያ እንዲከላከል ረድቷቸዋል፡፡

9. ከቆዳ አለርጂ ይጠብቃል፡- ኮረሪማ ፀረ ባክቴሪያ ንጥረነገር በውስጡ ስለያዘ ለቆዳ አለርጂ፣ ለቆዳ መሸብሸብና በቆዳ ላይ ለሚወጡ ጥቋቁር ነጠብጣቦች መፍትሔ የሚሰጥ ሲሆን በተለይ በሞቃታማ አካባቢዎች ስትሮክ የተሰኘውም በአንጎል ደም ቧንቧ ጥበት የሚከሰትን የደም ግፊት ይከላከላል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

ኮረሪማን በአነስተኛ መጠን መጠቀም ተገቢ ሲሆን ብዛት ያለው መጠን በምግብ ውስጥ ጨምሮ መጠቀም ግን የጨጓራ መቆጣትና የጨጓራ ቁስለት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለሆነም ጥንቃቄ ያሻል፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ share በማድረግ ይተባበሩን!

===============================

የስንፈተ-ወሲብን ለማከም

 ስለ ስንፈተ ወሲብ መፍትሄዎች ጠቃሚ ነው ያልነውን መረጃ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 6 መፍትሄዎች ሁሉም ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ የስንፈተ-ወሲብን ለማከም በሚል በጥናት የተረጋገጡ ናቸው፡፡ ስለምትከታተሉን ደስ ይለናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

6 የምግብ አይነቶች

1. እንቁላል

ቫይታሚን ዲ /Vitamin D/ የወሲብ ፍላጎትን ከሚጨምሩ ንጥረ ነገሮች ውስጥ የሚጠቀስ ሲሆን በቀን 2 የተቀቀለ እንቁላል መመገብ የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠንን ከፍ እንደሚያደርገው ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ በስንፈተ ወሲብ ዙሪያ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያስቀምጡትም የወንዶች ስንፈተ-ወሲብን ለመከላከል/ለማዳን ተጠቃሽ ከሆኑ ምግቦች መካከል እንቁላልን በግንባር ቀደምነት ያስቀምጡታል፡፡

 

2. ሙዝ

ሙዝ በውስጡ የወሲብ ስሜትን ከፍ የሚያደርግ በተለይም የወንዶች የወሲብ ስሜትን ከፍ የሚያደርግ “bromelain” የተሰኘ ኤንዛይም እንደያዘ ይገለፃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሙዝ አዘውትሮ መመገብ የወንዶች የብልት ፈሳሽ /sperm/ መጠን እንዲጨምር እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡

 

3. አጃ

አጃ በውስጡ ሴሮቶኒን (serotonin) የተባለ ኬሚካል የያዘ ሲሆን ይህም የጭንቀት መጠንን ይቀንሳል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙትም ስንፈተ-ወሲብ ከጭንቀት መጠን መጨመር ጋር የሚያያዝ ሲሆን ይህንን ጭንቀት በመጠኑ እንዲቀንስ በማድረግ አጃ ተጠቃሽ ነው፡፡ በተጨማሪም አጃ በውስጡ የሚገኘው የፕሮቲን መጠን ከፍተኛ በመሆኑ የአጃ ቅንጬ መመገብ በሰውነት ውስጥ የቴስቴስትሮን መጠን ከፍ እንዲል ያደርጋል፡፡

 

4. ጥቁር ቸኮሌት

በተመሳሳይ ጥቁር ቸኮሌት ስንፈተ-ወሲብን ከሚያሽሉ ምግቦች መካከል አንዱ ተደርጎ ይቀመጣል፡፡ በውስጡ የያዘው ንጥረ ነገር የደም ዝውውር ሂደትን የሚያነቃቃ ሲሆን “L-Arginine Hcl” የተባለው ንጥረ-ነገር በሰውነት ውስጥ የሆርሞን መመረትን ያቀላጥፋል፡፡

 

5. ካሮት

በቫይታሚኖች እንደተሞላ የሚነገርለት ካሮት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረነገሮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በካሮት ውስጥ ከሚገኙ ቫይታሚኖች መካከል አንዱ የወንዶች የብልት ጡንቻ እንዲጠነክር የሚያስችል ሲሆን በብልቱ አካባቢ የሚካሄደውን የደም ዝውውር ሂደት እንዲቀላተፍ ያደርጋል፡፡

 

6. አቮካዶ

አቮካዶ በውስጡ የተለያዩ ቫይታሚኖችን ማለትም ቫይታሚን ሲ፣ ኬ እና ቢ የመሳሰሉትን የያዘ ሲሆን በተለይም ቫይታሚን ኬ በሰውነት ውስጥ የደም ዝውውር በተገቢው የሰውነት ክፍል ላይ እንዲከናወን እንደሚያስችል ይገለፃል፡፡ በፕሮቲንና በፋይበርም የበለፀገ በመሆኑ አቮካዶ ተፈጥሯዊ የስንፈተወሲብ ማከሚያ ዘዴ እንዲሆን አስችሎታል፡፡

 

መልካም ጤንነት እንመኝሎታለን

++++++++++++++++++++++++++++++++

በተደጋጋሚ ቶሎ ቶሎ ሽንትዎ እየመጣ ተቸግረዋል?

 በምን ምክንያት እንደሆነ ያውቃሉ ?

      በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ማለት ጤናማ ከሚባለው የሽንት መምጫ ጊዜ በበለጠ በተደጋጋሚ ሽንት የመሽናት ፍላጎትን ሲለማመዱ/ ሲተገብሩ ነው፡፡ ይህ ልምድ በቀን ወይም በማታ ሊሆን ይችላል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ማታ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡

በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ሥራዎን፣ እንቅልፍዎንና አጠቃላይ ሠላምዎን ሊያስተጓጉል ይችላል፡፡ ስለዚህ የዚህን ችግር መነሻና ህክምናውን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ይሆናል ፡፡

👉 የዚህ ችግር መነሻ መንስኤ ምንድን ነው?

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን (Urinary Tract Infection)

በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በሆድና ዳሌ አካባቢ ህመም እንዲሁም ትኩሳት ካለብዎ በዚህ ኢንፌክሽን መጠትዎን አመላካች ናቸው፡፡

የስኳር በሽታ (Diabetes)

በተደጋጋሚ የመሽናት ፍላጎት ካለዎትና በጣም በርከት ያለ ሽንት የሚሸኑ ከሆነ በዓይነት አንድ ወይም ሁለት (Type 1 or 2) የስኳር በሽታ ተይዘው ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ሽንት የሚሸኑበት ምክንያት ሰውነትዎ ትርፍ ግሉኮስን ለማስወገድ ስለሚሞክር ነው፡፡

 

እርግዝና (Pregnancy)

በእርግዝና ወቅት ሽንት ቤትን በተደጋጋሚ መጎብኝት ይስተዋላል፡፡ ይህ ሁኔታ በደንብ የሚስተዋለው ደግሞ ጽንሱ በደንብ እየገፋ ይመጣና የሽንት ፌኛን ስለሚጫነው ነው፡፡

የፕሮስቴት ችግር (Prostate Problem)

ዩሬትራ ሽንትን ከሰውነታችን የሚያስወግድ ቱቦ ነው፡፡ ነገር ግን ፕሮስቴት በመጠን ይተልቅና ይህን ቱቦ ሊዘጋው ይችላል፡፡ ፕሮስቴት ዩሬትራን ይጫነዋል በተጨማሪም የሽንት ፌኛ ግድግዳን እንዲቆጣ ያደርገዋል ይህም የሽንት ፊኛ እንዲጨማደድ ስለሚያደርገው መያዝ ያለበትን ያክል ሽንት እንዳይዝ ስለሚያደርገው ለመሽናት እንቻኮላለን።

ኢንተርስቲሺያል ሲስታይቲስ (Interstitial Cystitis)

ይህ ችግር በምን እንደሚከሰት ግልጽ አይደለም ነገር ግን በሽንት ፌኛና ዳሌ አካባቢ ህመም ያስከትላል፡፡ ሽንት ለመሽናት ከመቻኮል በተጨማሪ ሌሎች ምልክቶችን ሊያዩ ይችላሉ፡፡

የሚያሸኑ መዳኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ (Diuretic Use)

ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚወስዷቸው ዳዩሪቲክስ መድሃኒቶች በተደጋጋሚ ሽንት እንዲሸኑ ሊደርግዎት ይችላሉ፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች ብዙ ውሃ ከኩላሊትና ከሰውነትዎ እንዲወገድ ይረዱናል፡፡

የነርቭ ጉዳት (Nerve Problems)

ወደ ሽንት ፊኛ የሚያመሩ ማንኛውም የነርቭ ጉዳት ሽንት በተደጋጋሚ እንዲሸኑ እንዲሁም ሽንትዎ በድንገት መቶ እንዲቻኮሉ ያስገድድዎታል፡፡

መልካም ጤንነት እንመኝሎታለን

============

ያለ እድሜያችን የሚከሰተው የፀጉር ሽበት ምክንያቱ ምንድን ነው? መፍትሄዎቹስ?

እድሜ እየገፋ ሲሄድ ሜላኒን የተባለ የቀለም መመረት እየቀነሰ ስለሚሄድ ፀጉራችን በተፈጥሯዊ መንገድ ወደ ነጭነት እየተቀየረ ይሄዳል። ስለሆነም ነጭ ፀጉር ከእድሜ መግፋት ጋር የሚያያዝ ይሆናል። ይሁን እንጂ ያለጊዜው የሚመጣ የፀጉር ቀለም ለውጥ (ሽበት) በአሁኑ ወቅት በለጋ እድሜ ላሉ ወጣቶች ጭምር አሳሳቢ ችግር እየሆነ መጥቷል። እናም ይህ ችግር የሚከሰትበትን ምክንያት ማወቅ የመፍትሄ አቅጣጫዎቹን ለመጠቆም ስለሚረዳ መነሻዎቹን እንመልከት።

1. ከባድ ጭንቀት

በመልካም የኑሮ ደረጃም ሆነ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኝ በህይዎት ጉዞው ውስጥ ደረጃው ቢለያይም ለጭንቀት የተጋለጠ ነው። ይህ በበርካታ ሃሳቦች የመዋጥና የመጨናነቅ ስሜት ከፍ ሲልም ያለጊዜው ለሚመጣ ሽበት ይዳርጋል።

2. ስነ ባህርይ (genetics)

ፀጉራችን ወደ ነጭነት የሚቀየርበት ጊዜ በዘርም ይወሰናል።

ስለሆነም አባቶቻችን አልያም አያቶቻችን ያለጊዜው በሚከሰት ሽበት ተጠቅተው ከነበረ እኛም በዚሁ ሂደት ውስጥ የማለፍ እድላችን ሰፊ ይሆናል።

3. ያልተመጣጠነ ምግብ

የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ለፀጉር ነጭ መሆን ምክንያት ይሆናል።

ለዚህም እንደ አሳ፣ የበግ ስጋ፣ እንቁላል፣ ቅቤ እና ወተት እና የወተት ውጤቶችን መጠቀም ካልተፈለገና ካለጊዜው ከሚመጣ የፀጉር ቀለም ለውጥ ይታደጋል ተብሏል።

4. መጥፎ ልማዶች

ሲጋራ ማጨስ፣ መጠጥ ማዘውተርና መሰል ያልተገቡ ልማዶች ለፀጉር መንጣት አስተዋፅኦ እንዳላቸውም ይነገራል።

5. ፈሳሽ ነገሮችን አብዝቶ መውሰድ

ሻይ፣ ቡና እና ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን ከልክ በላይ መውሰድም ለችግሩ በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።

መፍትሄዎቹስ?

1. የእግር ጉዞ

በጠዋት የሚደረግ የእግር ጉዞ ለመላው ጤንነታችንም ሆነ ለፀጉራችን ደህንነት ጠቃሚ መሆኑ ይነገራል።

በቀዝቃዛ ሳር ላይ በጠዋት በባዶ እግር መጓዝ ፀጉር ከተፈጥሯዊ ኡደቱ ውጭ ነጭ እንዳይሆን ያደርጋል ተብሎ ይታመናል።

2. ጭማቂዎችን መጠጣት

ትኩስ የአትክልትና ፍራፍሬ ጭማቂዎችን መጠጣት ስኳር ከሚጨመርባቸውና ከተለያዩ ለስላሳ መጠጦች እንድንርቅ ስለሚያደርግ ጥቅሙ የጎላ ነው።

በየቀኑ የካሮት ጭማቂ መጠጣት የፀጉርን ቀለም ወደ ነጭነት ከመቀየር ይታደጋል። የበቀለ ስንዴ ጭማቂም ለዚህ ችግር መፍትሄ አለው ነው የሚባለው።

3. የቫይታሚን ይዘት ያላቸውን ምግቦች መውሰድ

ከላይ እንደጠቀስነው የፀጉር ቀለም ካለጊዜው ወደ ነጭነት ለመቀየር የቫይታሚን ቢ12 እጥረት አንዱ ምክንያት ነው።

ስለሆነም በቫይታሚን ኤ እና ቢ የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር የሚያስፈልግ ሲሆን ሙዝ፣ ድንች፣ ጎመን፣ እርጎ፣ ስጋ፣ ጉበት እና የተለያዩ ጥራጥሬዎችን መመገብ ችግሩን ለማቅረፍ ይረዳል።

4. በአዮዲን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ

አሳ ከፍተኛ የአዮዲን ይዘት እንዳለው የሚነገር ሲሆን ሙዝ እና ካሮትም የተወሰነ አዮዲን ስለሚይዙ ብንመገባቸው የፀጉር መንጣት ለመከላከይ ይጠቅማሉ ተብሏል።

5. ሂና መቀባት

ሂና ወይም ሜሄዲ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በህንድ የፀጉርን ውበት ለመጠበቅ ጥቅም ላይ የዋለ እስካሁንም ድረስ የዘለቀ የፀጉር ቀለም ነው። ሂናን ሻወር ከወሰድን ከአንድ ስአት በኋላ ብንጠቀመው ውጤታማ እንደሚሆን ይነገራል። ሂና የፀጉርን ጥንካሬን በማሳደግ ሽበትንም ይከላከላል።

6. ዘይት መቀባት

የዘንባባና የለውዝ ዘይት እንዲሁም የሎሚ ጭማቂ የፀጉር ቀለም መንጣትን ለመከላከል ከድሮ ጀምሮ ጥቅም ላይ ውለዋል።

ሰሊጥ መመገብ ወይም ጭንቅላትን የሰሊጥ ዘይት መቀባትም ፀጉርን ጥቁር ለማድረግ እንደሚያግዝ ይነገራል።

7. ጭንቀትን ማስወገድ

ጭንቀት ለምንም ነገር መፍትሄ ሆና አያውቅም፤ ለሌላ ከባድ ችግር ያጋልጣል እንጅ። ስለሆነም ላልተገባ የፀጉር ቀለም መለወጥ እና ለሌላ የጤና እክል ከመዳረግ ይልቅ በተረጋጋ ሁኔታ ለችግሮች መፍትሄ መስጠቱ ይበጃል።

8. ከመጥፎ ልማዶች መራቅ

ከላይ እንደጠቀስነው እንደ ሲጋራ ማጨስ፣ የአልኮል መጠጦችን ማዘውተር፣ የአደንዛዥ እፅ የመጠቀም መጥፎ ልማዶችን ማስወገድም ለጤናማ ህይዎትና ለፀጉር ደህንነት ወሳኝ በመሆኑ ከእነዚህ ልማዶች መራቅ ያስፈልጋል። በተጨማሪም የሂና ፓውደር፣ የናና ጭማቂ፣ ቡና እና እርጎን በማዋሃድ በየሳምንቱ ለሶስት ስአታት ፀጉርን በመቀባት እና በሻምፖ መታጠብም ጥሩ ውጤት ያስገኛል ።

የፀጉር መርገፍን ለመከላከል የሚጠቅሙ ነገሮች !

• ትክክለኛ አመጋገብ ይኑርዎት፦ ፕሮቲን፣ ብረት (Iron) እና ሌላ ንጥረ ነገሮች ያካተተ ምግብ መመገብ ጠቃሚ ነው።

• ጭንቀትን ማስወገድ፦ ጭንቀት በተለያየ መልኩ ሰውነትን የሚጎዳ ሲሆን፤ የፀጉር መርገፍን ያስከትላል።

• ቫይትሚኖችን መውሰድ፦ የፀጉር መርገፍ በሰውነት ውስጥ የቫይታሚን ማነስን ስለሚያሳይ እንደ ቫይታሚን ሲ፣ ቢ፣ ኢ፣ ኤ፣ ዲ፣ ባዮቲን እና ዚንክ የመሳሰሉትን መውሰድ ይጠቅማል::

• የሙቀት ጉዳትን ይከላከሉ፦ ከተለያየ የፀጉር ማስዋቢያ እቃዎች እንደ ፀጉር ማድረቂያ፣ ፀጉር መጠቅለያ እና የፀጉር ካውያ የሚወጣው ሙቀት ፀጉር ላይ ጉዳት ያስከትላል።

• መጥፎ ጸጉር ግብአቶችን ያስወግዱ፦ የፀጉር ቀለም፣ ፐርም፣ ረላክሰር፣ ስፕሬይ፣ መጥፎ ሻንፖ እና ኮንዲሽነር ወይም የፀጉር ተፈጥሯዊ ፕሮቲን እና ዘይቶችን ሊጎዱ የሚችሉ ማንኛውም ግብአቶችን ማስወገድ።

• ፀጉርን ወደታች ማድረግ፦ ውጥር አድርጎ ወደላይ ማስያዝ፣ ሙጥጥ አድርጎ ወደኋል ማስያዝ፣ ብዙ ጄል ማድረግ እና ፀጉር ወደኋል በጣም መጎተት የፀጉር መርገፍን ያባብሳል።

bottom of page